ናሚቢያ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ

የናሚቢያ ሪፑብሊክ
Republic of Namibia

የናሚቢያ ሰንደቅ ዓላማ የናሚቢያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የናሚቢያመገኛ
ዋና ከተማ ዊንድሁክ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛአፍሪካንስ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ሂፊከፑኘ ፖሃምባ
ናሃስ አንጉላ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
825,418 (33ኛ)
ገንዘብ የናሚቢያ ዶላር
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +264


ናሚቢያ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስሜን በአንጎላና በዛምቢያ፣ በምስራቅ በቦትስዋና፣ በደቡብም በደቡብ አፍሪቃ ትካለላለች። በ1982 አመተ ምኅረት ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪቃ ስላገኘች በጣም አዲስ አገር ነች። ዋና ከተማዋ ዊንድሁክ ነው።

ታሪክ[ለማስተካከል]

የናሚቢያ በረኅ አውራጃ ከጥንት ጀምሮ በሳን (ቡሽማን)፣ በዳማራና በናማቋ ሕዝቦች ተሰፈረ። በ14ኛው መቶ ዘመን፣ የባንቱ ወገኖች ባስፋፉ ጊዜ አገሩን ሠፈሩ። ክልሉ ግን ከ19ኛው መቶ ዘመን በፊት በአውሮጳውያን አልተዘለቀም። በዚያን ጊዜ ጀርመን ደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ አገሪቱ የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። ዳሩ ግን ዋልቪስ በይ የተባለው ትንሽ ወደብ ብቻ የእንግሊዝ ግዛት ነበር።