ጀርመን
ቡንደስረፑብሊክ Deutschland |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ዶይችላንድሊድ | ||||||
ዋና ከተማ | በርሊን |
|||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ጀርመንኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዚዳንት ቻንስለር |
ክርስትያን ቩልፍ አንጌላ መርክል |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
357,021 km2 (63ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ዩሮ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | +49 |
ጀርመን ወይንም በይፋ ስሙ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛ አውሮፓ የሚገኝ ታሪካዊ አገር ነው። አገሩ 16 ክልሎች ሲኖሩት ዋናና ትልቁ ከተማውም በርሊን ነው።
ባህልና ጠቅላላ መረጃ[ለማስተካከል]
ጀርመን አንድ ይፋዊ ቋንቋ ብቻ አለው እርሱም ጀርመንኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የጀርመንኛ ቀበሌኞች በአገሩ ይገኛሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ጀርመን «የገጣሚዎችና የአሳቢዎች አገር» በመባል ታውቋል። በዓመታት ላይ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በፍልስፍና፣ በሙዚቃ፣ በሲኒማ፣ እና በሳይንስ ዘርፎች በርካታ አስተዋጽኦች በማቅረባቸው ጀርመናውያን በዓለም ዝነኛነት አገኝተዋል፤ እንዲሁም መኪና የሚባለውን ፈጠራ በማስለማት ፈር ቀዳጅ ሆኑ። ጀርመን ደግም ስለ ቋሊማና ቢራዎች ልዩነት ብዛት የገነነ ሆኗል። እግር ኳስ በጀርመን ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው።
የራይን ወንዝ አቅራቢያ በጥንት ከሁሉ በፊት የተሰፈረው ሲሆን እዚያ አንዳንድ ጥንታዊ የሮሜ መንግሥት ድልድይ፣ አምባ፣ ወይም ፍርስራሽ ሊታይ ይችላል። የጀርመን ሕዝብ በብዛት ክርስቲያኖች ናቸው፤ በስደትም ወደ አገራቸው ለደረሱት ሰዎች በጠቅላላው ሰላምታ ሰጪዎች ናቸው። የበርሊን ግድግዳ በፈረሰበትና «የቅዝቃዛ ጦርነት» በጨረሰበት ወቅት የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ ተከሠተ። በዚያ ሰዓት የቀድሞ አገራት ምሥራቅ ጀርመንና ምዕራብ ጀርመን አብረው የአሁኑን ጀርመን መንግሥት ፈጠሩ።
ብዙ የጀርመን ሰዎች በዓለም ዙሪያ ስመ ጥሩ ናቸው። ይህም ደራሲዎች ያኮብ ግሪምና ወንድሙ ቭልሄልም ግሪም፣ ባለቅኔው ዮሐን ቩልፍጋንግ ቮን ጌጠ፣ የፕሮቴስታንት ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉጠር፣ ፈላስፋዎች ካንት፣ ኒሺና ሄገል፣ ሳይንቲስቱ አልቤርት አይንስታይን፣ ፈጠራ አፍላቂዎች ዳይምለር፣ ዲዝልና ካርል ቤንዝ፣ የሙዚቃ ቃኚዎች ዮሐን ሴባስትያን ባክ፣ ሉድቪግ ቫን ቤትሆቨን፣ ብራምዝ፣ ስትራውስ፣ ቫግነርና ብዙ ሌሎች ይከትታል።
እጅግ ቁም ነገር የሆነ ጠቃሚ ፈጠራ ማሳተሚያ ዮሐንስ ጉተንቤርግ በሚባል ሰው በ1431 ዓ.ም. ተጀመረ። ስለዚህ በቅርብ ጊዜ፣ ተጓዦች ከውጭ አገር ሲመልሱ በአውሮፓ ያለው ሰው ሁሉ እርግጡን ያውቀው ነበር። አሁን ጀርመን «ዶይቸ ቨለ» በሚባል ራዲዮን ጣቢያ ላይ ዜና በእንግሊዝኛ ያሠራጫል። የጀርመን ሕዝብ ባማካኝ ከአውሮፓ ሁሉ ቴሌቪዥንን የሚወድዱ ሲሆኑ ፺ ከመቶ ሰዎች ወይም ሳተላይት ወይም ገመድ ቴሌቪዥን አላቸው።
በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ አገሮች |
ምሥራቃዊ አውሮፓ - ቤላሩስ|ቡልጋሪያ|ሞልዶቫ|ሮማንያ|ሩሲያ|ዩክሬን |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ! |