ዴሞክራሲ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ

ዴሞክራሲ ወይም ዴሞክራሲያዊ መንግስት፡ የመንግስት መዋቅር አይነት ነው። በህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ (ቀጥተኛ ዴሞክራሲ) ወይም በህዝብ በተመረጡ አካላት (ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ) በመባል ይከፈላል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው። እንግዲህ ዲሞክራሲያ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን (የፓርላማ ዓባላትን) ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ። በዚህ ሥርዓት ብዙኃኑ መንግሥት የማዋቀር መብት አለው። ቢሆንም የጥቂቶች ሙሉ መብት በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም የዜጎች መብት ማለትም የሰው ልጅ መብትና ነፃነት፣ እኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ፣ እና ሌሎችንም ማክበር የዲሞክራሲ አስተዳደር (አገዛዝ) መርሆች ናቸው።

ታሪክ[ለማስተካከል]

ዴሞክራሲ የመጣው የግሪክ ቃል ከሆኑት «ዴሞስ» ማለት «ህዝብ» እና «ክራቶስ» ማለት «ስልጣን» የመጣ ቃል ነው። በጥንታዊ የግሪክ ከተማ አቴንስ አገዛዝ ይተገበር ነበር።