Gambella Regional State Gambella Regional State

Flag of Gambella Regional Stateየጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሁለት ዞኖችንና ስምንት ወረዳዎችን አካቷል፡፡

ርዕሰ ከተማ

የክልሉ ርዕሰ ከተማ ጋምቤላ ነው፡፡

የስፍራው አቀማመጥ

ክልሉ በኢትዩጵያ ምእራባዊ ጫፍ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ በምእራብ ደቡብና ሰሜን ሱዳንን ሲያዋስን፣ በደቡብና በምስራቅ ደግሞ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን ያዋስናል፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜንና ምስራቅ ያዋስኑታል፡፡

የቆዳ ስፋት

ክልሉን በቅርቡ የተቀላቀለውን ወረዳ ሳይጨምር የክልሉ የቆዳ ስፋት 25‚274 ኪ.ሜ ይደርሳል፡፡

ስነ-ህዝብ

በ1987 በተደረገው የህዝብ ቆጠራ መስረት፣ የህዝብ ብዛቷ 182.862 ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 92‚090 የሚሆነው ወንዶች ሲሆን 88‚960 ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ 153‚438 /84.9%/  የሚሆነው ህዝብ በክልሉ በገጠራማ ቦታዎች ውስጥ የኖራል፡፡ ዋና ዋናዎቹ የክልሉ ብሄረሰቦች ኑዌር፣ አኙዋክ፣ መዘንገር፣ አፓና እና ኮሞ ይባላሉ፡፡ በተጨማሪም የኦሮሞ፣ አማራ፣ ከምባታ፣ ከፉ፣ ትግሬ እና ሌሎችም ብሄረሰቦች በክልሉ ይኖራሉ፡፡ ከጠቅላላው የህዘብ ስብጥር 46 ከመቶ ኑዌር፣ 27 ከመቶ አኙዋክ፣ 8 ከመቶ አማራ 6 ከመቶ ኦሮሞ፣ 5.8 ከመቶ መዠንገር፣ 4.1 ከመቶ ከፋ ፣ 2 ከመቶ ሞካ ፣ 1.6 ከመቶ ትግሬ እና 5.5 ከመቶ የሚሆነው ደግሞ ከደቡብ ህዝቦች ናቸው፡፡ አማርኛ የክልሉ የስራ ቋንቋ ነው፡፡ ህዝቡ ተቻችሎና ተደጋግፎ በመኖር የሚታወቅ ሲሆን፣ የተለያዩ እምነት ተከታዬች የሚኖሩበት ክልል ነው፡፡ 44 ከመቶ የኘሮቴስታንት፣ 24.1 ከመቶ የኦርቶዶክስ፣ 10.3 ከመቶ የባህላዊ ሀይማኖት ፣ 5.1 ከመቶ የእስልምና፣ 3.2 ከመቶ የካቶሊክ እና 12.7 ከመቶ የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ይኖሩበታል፡፡

 

Pages: 1  2